ዶሚኒክ ሶቦስላይ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለአምስተኛ ጊዜ የሊቨርፑል የስታንዳርድ ቻርተርድ የወንዶች የወሩ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል።
በክለቡ ይፋዊ ድረ-ገጽ (Liverpoolfc.com) ላይ በደጋፊዎች መካከል በተካሄደው የህዝብ ድምፅ አሰጣጥ መሠረት፣ ሀንጋሪያዊው አማካይ የመጋቢት ወር (ከየካቲት 22 – መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም.) የክብር ሽልማት ባለቤት ሆኗል።
ሶቦስላይ ከጠቅላላው ድምፅ ወደ ሁለት-ሶስተኛ የሚጠጋውን በማግኘት ቀዳሚ ሲሆን፣ የቡድን አጋሮቹ መሐመድ ሳላህ እና ሚሎስ ከርኬዝ እንደ ቅደም ተከተላቸው ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በመጋቢት ወር ሊቨርፑል ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ላይ ሶቦስላይ በአማካይ ስፍራ እና በቀኝ መስመር ተከላካይነት ተሰልፎ ሁሉንም ደቂቃዎች የተጫወተ ሲሆን፣ በሁለቱ ጨዋታዎች ላይ ደግሞ ግብ ማስቆጠር ችሏል።
- በአንፊልድ ከቶተንሃም ሆትስፐር ጋር በተደረገው ጨዋታ፣ ቁጥር 8ቱ ተጫዋች በዘንድሮው የፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን አራተኛውን የቅጣት ምት ግብ አስቆጥሯል። ይህም በአንድ የውድድር ዘመን በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ ከፍተኛውን የቅጣት ምት ግብ ያስቆጠረ የሊቨርፑል ተጫዋች አድርጎታል።
- ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሊቨርፑል ጋላታሳራይን ሲያሸንፍ፣ ከማዕዘን ምት የተሻገረለትን ኳስ በአስደናቂ ሁኔታ መረብ ላይ በማሳረፍ ለአርኔ ስሎት ቡድን ወሳኝ ግብ አበርክቷል።
የ2017-18 የውድድር ዘመን የወሩ ምርጥ ተጫዋች አሸናፊዎች ዝርዝር፦
- መጋቢት፦ ዶሚኒክ ሶቦስላይ
- የካቲት፦ ዶሚኒክ ሶቦስላይ
- ጥር፦ ፍሎሪያን ዊርትዝ
- ታህሳስ፦ ሁጎ ኤኪቲኬ
- ህዳር፦ ዶሚኒክ ሶቦስላይ
- ጥቅምት፦ ዶሚኒክ ሶቦስላይ
- መስከረም፦ ፌዴሪኮ ቺዬዛ
- ነሐሴ፦ ዶሚኒክ ሶቦስላይ
አስተያየት ይስጡን