የቀድሞው የቼልሲ ኮከብ ጆ ኮል፣ አሌሀንድሮ ጋርናቾ በክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ማግኘት ከፈለገ በጥንቃቄ መንቀሳቀስ እንዳለበት አስጠነቀቀ።
ጋርናቾ ባለፈው ክረምት በ40 ሚሊዮን ፓውንድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ካመራ በኋላ እስካሁን ስኬታማ መሆን አልቻለም፤ በአሁኑ ወቅትም በከፍተኛ የብቃት መውረድ ላይ ይገኛል። ይህ የ21 ዓመት ተጫዋች አንዳንድ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎችን ቢያሳይም፣ በቋሚነት ጥሩ ብቃት ለማሳየት ተቸግሯል። በዚህ የውድድር ዘመን የተቃዋሚ ቡድን ደጋፊዎች በተደጋጋሚ ሲያፏጩበት መቆየታቸውም የዘወትር ትዕይንት ሆኗል።
የቀድሞው የቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ሊያም ሮዜኒየር ይህ የሚሆነው ጋርናቾ ለተቃዋሚዎች “አደገኛ” ስለሆነ ነው ቢሉም፣ ሌሎች ግን ጋርናቾ በፕሪሚየር ሊጉ ተወዳጅ ለመሆን በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ባሉበት ችግሮች ምክንያት እንደሆነ ያምናሉ።
ለፓዲ ፓወር (Paddy Power) አስተያየቱን የሰጠው የቀድሞው የብሉዝ የመስመር ተጫዋች ጆ ኮል እንዲህ ብሏል፦
“ጋርናቾ ምርጥ ተጫዋች ሊሆን እንደሚችል የሚያሳዩ ምልክቶች ሁልጊዜም አሉ። ነገር ግን በአሌሀንድሮ ዙሪያ አንዳንድ ጊዜ የሚነሱ ወሬዎች እንቅፋት ሊሆኑበት ይችላሉ። በዚህ የውድድር ዘመን ብዙም የሚባል ነገር ባይኖርም፣ ከቀድሞ ክለቡ (ማንቸስተር ዩናይትድ) ጋር በተያያዘ የነበሩ ታሪካዊ ቅሬታዎች ስላሉ፣ እንደ ተጫዋች ስርዓትን ጠብቆ መጓዝ ይኖርበታል።”
ኮል አክሎም ጋርናቾ የተሻለ ተጫዋች ለመሆን ትልቅ ዕድል እንዳለው ጠቁሞ፣ ነገር ግን በራሱ ማመን እና በትክክለኛው መንገድ ላይ ለመጓዝ መፈለግ እንዳለበት ገልጿል። “ይህ በራሱ እና በአዲሱ አሰልጣኝ ላይ የተመሰረተ ነው። አዲሱ አሰልጣኝ ሲመጣ ጋርናቾ በእቅዱ ውስጥ ምን ቦታ ይኖረዋል?” ብሏል።
ከ2003 እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) ባለው ጊዜ ውስጥ ከቼልሲ ጋር ሰባት ዋንጫዎችን ያሸነፈው ኮል ሲቀጥል፦ “እኔ ብመክረው ደስተኛ የሚሆንበትና የሚረጋጋበት ቤት (ክለብ) መፈለግ አለበት እለዋለሁ። የቼልሲ ደጋፊዎች በአሁኑ ወቅት በእሱ ላይ ጥቂት ቅሬታ አላቸው፤ እኔም ጥሩ እየተጫወተ አለመሆኑን እስማማለሁ። ነገር ግን በጣም መጥፎ የሚባል አይደለም፤ ዝም ብሎ በምርጥ ብቃቱ ላይ አይደለም እንጂ።”
አስተያየት ይስጡን