ሚኬል አርቴታ አርሰናል በፕሪምየር ሊግ የሚያጋጥመው ፉክክር፣ ባየር ሙኒክ በቦንደስሊጋ እና ፒኤስጂ በሊግ 1 ካላቸው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር ልዩነቱ “እንደ ሰማይና ምድር” (night and day) እንደሆነ ያምናል።
አርሰናል በሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታው ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር 1 ለ 1 ሲለያይ፣ በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ደግሞ ፒኤስጂ ባየር ሙኒክን 5 ለ 4 ባሸነፈበት አስደሳች ጨዋታ ተመልክተናል።
የፕሪምየር ሊግ ቡድኖች እንዲህ አይነት አስደሳች ጨዋታ ማቅረብ ይችላሉ ወይ ተብሎ ሲጠየቅ፣ አርቴታ ፒኤስጂ እና ባየር ሙኒክ ከአርሰናል አንጻር አላቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ብልጫዎች ጠቁሟል። “ያንን የባየር እና የፒኤስጂ ጨዋታ ስመለከት፣ በሁለቱ ቡድኖች ጥራት እና በተለይም ተጫዋቾቹ ባሳዩት የግል ብቃት ረገድ እስካሁን ካየኋቸው ጨዋታዎች ሁሉ ምርጡ ሊሆን ይችላል” ሲል አስረድቷል።
“እንዲህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም። ነገር ግን ተጫዋቾቹ ሜዳ ላይ ያሳለፉትን ደቂቃ እና ያላቸውን ትኩስነት (freshness) ስመለከት አልተገረምኩም። እንዲህ አይነት ጥራት ያላቸውን አጋጣሚዎች ለመፍጠር በጣም ትኩስ መሆን ያስፈልጋል፤ በሊጎቹ መካከል ያለው ልዩነት እና የሚወዳደሩበት መንገድ እንደ ሰማይና ምድር ነው” ብሏል።
አክሎም፦ “በቅርቡ የወጡ በርካታ አሃዛዊ መረጃዎችን (stats) ማየት ብቻ ይበቃል። ስለዚህ እኛ እየተወዳደርን ያለነው በሁለት የተለየ ዓለም ውስጥ ነው፤ አንዱን ወገን ያለ ሌላኛው አውድ (context) ማወዳደር አይቻልም። ይህ ፍትሃዊ ነው ብዬ አላስብም” ሲል ገልጿል።
አስተያየት ይስጡን